መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ከፍራንክሊን ግርሃም ጋር በኢትዮጵያ የሚደረገው በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም ነው። በዕለቱ የስብከተ ወንጌል መልዕክት በወንጌላዊ ፍራንክሊን ግርሃም ይቀርባል፤ እንዲሁም የአምልኮና የዝማሬ መርሐ ግብር ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት በመጡ መዘምራን ይከናወናል። በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ፕሮግራሙን ለማሳካት ልዩ የሆነ የወንጌል ምስክርነት ለማህበረሰቡ ያደርጋሉ። ለአንድ አማኝ ላልሆነ አዲስ ሰው በመጸለይ ወደዚህ የመለኮታዊ ገብኝት መርሐ ግብር መጋበዝዎን አይዘንጉ።
የካቲት 1 እና 2 ቀን 2017 ዓ/ም