መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ከፍራንክሊን ግርሃም ጋር

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ከፍራንክሊን ግርሃም ጋር

ስለወደፊቱ ጭንቀት፥ ፍርሃት ወይም አለመረጋጋት ይሰማዎታል? የካቲት 29 እና 30 ፍራንክሊን ግርሃም ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ የሚያስተላልፉትን በልብዎ እውነተኛ ሰላም እንዴት እንደሚያገኙ የሚያቀርቡትን መልዕክት በቀጥታ ይከታተሉ - ቀጣይ ቀናትዎን በተስፋ ይጀምሩ።

ይመልከቱ፥ መጽናናት ለሚያስፈልገው ሰው ያካፍሉ፥ በምስራቅ አፍሪካ/በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በ3 ሰአት ይጀምራል።


የምስራች !

እግዚአብሔር ለኃጢአትህ እንዲሞት አንዲያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እስኪሰጥ ድረስ እጅግ ወዶሃል። በእርሱ ብታምን፥ ከኃጢአትህ ብትመለስና ኢየሱስን የሕይወትህ ጌታ ብታደርግ፥ ያኔ ከእርሱ ጋር በሰማይ ልትኖር የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ።

ይህንን ጸሎት ዛሬ ትጸልያለህ?

አምላኬ ሆይ፥

እኔ ኃጢአተኛ እንደሆንሁ አውቃለሁ። ከኃጢአቴ መመለስ እፈልጋለሁና ይቅርታህን እንድታደርግልኝ እለምናለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ልጅህ እንደሆነ አምናለሁ። ለኃጢአቴ እንደሞተና አንተ ከሞት እንዳስነሳኸው አምናለሁ። እርሱ ወደ ልቤ እንዲገባና ሕይወቴን እንዲቆጣጠር እፈልጋለሁ። ከዛሬ ጀምሮ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኜ ላምንና እንደ ጌታዬ ልከተለው እፈልጋለሁ።

በኢየሱስ ስም፥ አሜን።

ከዚህ በኃላስ?

ጌታ ኢየሱስን ለመቀበልና ከእርሱ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ጸልየዋል? በሕይወትዎ እንዲያድጉ እንዲረዳዎ በድረ ገጽ የሚገኙ ጥቂት ጽሑፎችን ለመስጠት እንፈልጋለን። ለመጀመር ከታች ያለውን “አዎን፥ እጸልያለሁ” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ይጠቀሙ።

ጥያቄ አልዎ? ጥያቄዎን ለማቅረብና አንድ ሰው እንዲያናግርዎ ከታች ያለውን ቁልፍ ይጠቀሙ።